bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 19
Job 19
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2
“ነፍሴን የምታስጨንቋት፣ በቃልስ የምትደቍሱኝ እስከ መቼ ነው?
3
እነሆ፤ ዐሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ ያለ ዕፍረትም በደላችሁኝ።
4
በእውነት ተሳስቼ ከሆነ፣ ስሕተቱ የራሴ ጕዳይ ነው።
5
ነገር ግን ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ብታደርጉ፣ መዋረዴንም እኔን ለመሞገት ብትጠቀሙበት፣
6
እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፣ በመረቡም እንደ ከበበኝ ዕወቁ።
7
“ ‘ተበደልሁ’ ብዬ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ባሰማም፣ ፍትሕ አላገኝም።
8
እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቷል፤ መሄጃዬንም በጨለማ ጋርዷል።
9
ክብሬን ገፍፎኛል፤ ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወስዷል።
10
እስክወገድ ድረስ በሁሉ አቅጣጫ አፈራርሶኛል፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቅሎታል።
11
ቍጣው በላዬ ነድዷል፤ እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል።
12
ሰራዊቱ ገፍተው መጡ፤ በዙሪያዬ ምሽግ ሠሩ፤ ድንኳኔንም ከብበው ሰፈሩ።
13
“ወንድሞቼን ከእኔ አርቋል፤ ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።
14
ዘመዶቼ ትተውኛል፤ ወዳጆቼም ረስተውኛል።
15
የቤቴ እንግዶችና ሴት አገልጋዮቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ እንደ ባዕድም ተመለከቱኝ፤
16
አገልጋዬን ብጣራ፣ በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም።
17
እስትንፋሴ ለሚስቴ እንኳ የሚያስጠላት ሆነ፤ የገዛ ወንድሞቼም ተጸየፉኝ።
18
ሕፃናት እንኳ ይንቁኛል፤ ባዩኝም ቍጥር ያላግጡብኛል።
19
የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸውም በላዬ ተነሡ፤
20
ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
21
“ወዳጆቼ ሆይ፤ ራሩልኝ፤ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ዕዘኑልኝ።
22
እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ ለምን ታሳድዱኛላችሁ? አሁንም ሥጋዬ አልበቃችሁምን?
23
“ምነው ቃሌ በተጻፈ ኖሮ! በመጽሐፍም በታተመ!
24
ምነው በብረትና በእርሳስ በተጻፈ ኖሮ! በዐለትም ላይ በተቀረጸ!
25
የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፣ በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ።
26
ቈዳዬ ቢጠፋም፣ ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤
27
ሌላ ሳይሆን እኔው በገዛ ዐይኔ፣ እኔ ራሴ አየዋለሁ፤ ልቤ በውስጤ ምንኛ በጉጉት ዛለ!
28
“ ‘የችግሩ መንሥኤ በውስጡ አለ፤ እኛ እንዴት እናሳድደዋለን?’ ብትሉ፣
29
ቍጣ በሰይፍ መቀጣትን ያስከትላልና፣ ራሳችሁ ሰይፍን ፍሩ፤ በዚያን ጊዜ ፍርድ እንዳለ ታውቃላችሁ።”
← Chapter 18
Chapter 20 →