bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 20
Job 20
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ናዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤
2
“እጅግ ታውኬአለሁና፣ ሐሳቤ መልስ እንድሰጥ ይጐተጕተኛል።
3
የሚያቃልለኝን ንግግር ሰምቼአለሁ፤ መልስም እሰጥ ዘንድ መንፈሴ ገፋፋኝ።
4
“ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ ጊዜ ጀምሮ፣ ከጥንቱ እንዴት እንደ ነበረ ታውቃለህን?
5
የኀጢአተኞች መፈንጨት ለዐጭር ጊዜ፣ የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?
6
እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ቢልም፣ ዐናቱም ደመናትን ቢነካ፣
7
እንደ ኵበት ለዘላለም ይጠፋል፤ ቀድሞ ያዩትም፣ ‘የት ገባ?’ ይላሉ።
8
እንደ ሕልም በርሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤ እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።
9
ቀድሞ ያየው ዐይን ዳግመኛ አያየውም፤ የነበረበትም ቦታ ከእንግዲህ አይመለከተውም።
10
ልጆቹ ለድኾች ካሳ መክፈል አለባቸው፤ እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል።
11
ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ ከእርሱ ጋር በዐፈር ውስጥ ይተኛል።
12
“ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣ ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣
13
አውጥቶ ለመጣል እየሳሳ፣ በአፉ ውስጥ ቢያቈየው፣
14
ምግቡ በሆዱ ውስጥ ይመርራል፤ በውስጡም እንደ እባብ መርዝ ይሆናል።
15
የዋጠውን ሀብት ይተፋል፤ እግዚአብሔርም መልሶ ከሆዱ ያወጣዋል።
16
የእባብ መርዝ ይጠባል፤ የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።
17
ማርና ቅቤ በሚያፈስሱ ጅረቶች፣ በወንዞችም አይደሰትም።
18
የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤
19
ድኾችን በመጨቈን ባዶ አስቀርቷቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቋል።
20
“ክፉ ምኞቱ ዕረፍት አይሰጠውም ሀብቱም ሊያድነው አይችልም።
21
ያለውን አሟጥጦ ስለሚበላ፣ ዘላቂ ብልጽግና አይኖረውም።
22
በተድላ መካከል እያለ ጕስቍልና ይመጣበታል፤ በከባድ መከራም ይዋጣል።
23
ሆዱን በሞላ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሚነድድ ቍጣውን ይሰድበታል፤ መዓቱንም ያወርድበታል።
24
ከብረት መሣሪያ ቢሸሽም፣ የናስ ቀስት ይወጋዋል።
25
ቀስቱን ከጀርባው፣ የሚያብለጨልጨውንም ጫፍ ከጕበቱ ይመዝዛል፤ ፍርሀትም ይይዘዋል፤
26
ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ተዳርጓል፤ ሰው ባላራገበው እሳት ይበላል፤ በድንኳኑም ውስጥ የተረፈውን ይልሳል።
27
ሰማያት ኀጢአቱን ይገልጡበታል፤ ምድርም ትነሣበታለች፤
28
በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን ቤቱን ጐርፍ፣ መኖሪያውንም ወራጅ ውሃ ይወስድበታል።
29
እግዚአብሔር ለኀጢአተኞች የወሰነው ዕድል ፈንታ፣ ከአምላክም ዘንድ የተመደበላቸው ቋሚ ቅርስ ይህ ነው።”
← Chapter 19
Chapter 21 →