bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 17
Job 17
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
መንፈሴ ደክሟል፣ ዘመኔ ዐጥሯል፤ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
2
አላጋጮች ከብበውኛል፤ ትኵረቴም ትንኰሳቸው ላይ ነው።
3
“እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ?
4
እንዳያስተውሉ ልባቸውን ይዘሃል፤ ስለዚህ ድል አትሰጣቸውም።
5
ለጥቅም ሲል ወዳጁን የሚያወግዝ፣ የልጆቹ ዐይን ይታወራል።
6
“እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ።
7
ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤ መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።
8
ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ።
9
ጻድቃን ግን በያዙት መንገድ ይጸናሉ፤ ንጹሕ እጅ ያላቸውም እየበረቱ ይሄዳሉ።
10
“ነገር ግን እናንተ ሁላችሁ፣ እስቲ ተመልሳችሁ እንደ ገና ሞክሩ! ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም።
11
ዕድሜዬ ዐለቀ፤ ዕቅዴም ከሸፈ፤ የልቤም ሐሳብ ከንቱ ሆነ።
12
እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ጨልሞም እያዩ፣ ‘ብርሃን ቀርቧል’ ይላሉ።
13
ተስፋ የማደርገው ቤት መቃብር ብቻ ከሆነ፣ መኝታዬንም በጨለማ ካነጠፍሁ፣
14
መበስበስን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ትልንም፣ ‘አንቺ እናቴ’ ወይም ‘እኅቴ ነሽ’ ካልሁ፣
15
ታዲያ፣ የእኔ ተስፋ ወዴት ነው? ተስፋዬን የሚያይልኝስ ማን ነው?
16
ወደ ሞት ደጅ ይወርዳልን? አብረንስ ወደ ትቢያ እንሄዳለንን?”
← Chapter 16
Chapter 18 →