bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 16
Job 16
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2
“ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ እናንተ ሁላችሁ የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ።
3
ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን? ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው?
4
እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣ እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ ቃላት አሳክቼ በመናገር፣ በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር።
5
ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣ የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር።
6
“ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ ዝም ብልም አይተወኝም።
7
እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል።
8
ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።
9
በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ ጥርሱን ነከሰብኝ፤ ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ።
10
ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤ በንቀት ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።
11
እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በጠማሞችም እጅ ጣለኝ።
12
በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤
13
የእርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈስሳል።
14
ደጋግሞ ይቀጠቅጠኛል፤ እንደ ጦረኛም ተንደርድሮ ይመጣብኛል።
15
“በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ ክብሬን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።
16
ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቷል፤ ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፏል፤
17
ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
18
“ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ!
19
አሁን እንኳ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ ጠበቃዬም በላይ በአርያም ይገኛል።
20
ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል።
21
ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ!
22
“ከጥቂት ዓመታት በኋላ፣ ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።
← Chapter 15
Chapter 17 →