bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 13
Job 13
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
“ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቷል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ፤
2
እናንተ የምታውቁትን፣ እኔም ዐውቃለሁ፤ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።
3
ነገር ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀሥ እሻለሁ።
4
እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።
5
ምነው ዝም ብትሉ! ያ ከጥበብ ይቈጠርላችሁ ነበር።
6
እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፤ የከንፈሬንም አቤቱታ አድምጡ።
7
ለእግዚአብሔር ብላችሁ በክፋት ትናገራላችሁን? ስለ እርሱስ በማታለል ታወራላችሁን?
8
ለእርሱ ታደላላችሁን? ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን?
9
እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነገር ይገኝባችኋልን? ሰውን እንደምታታልሉ፣ ልታታልሉት ትችላላችሁን?
10
በስውር አድልዎ ብታደርጉ፣ በርግጥ እርሱ ይገሥጻችኋል።
11
ግርማው አያስደነግጣችሁምን? ክብሩስ አያስፈራችሁምን?
12
ምሳሌዎቻችሁ የዐመድ ምሳሌዎች ናቸው፣ መከላከያችሁም የጭቃ ምሽግ ነው።
13
“ዝም በሉ፤ እኔ ልናገር፤ የመጣው ይምጣብኝ።
14
ሥጋዬን በጥርሴ፣ ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ?
15
ቢገድለኝም እንኳ በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ስለ መንገዴም ፊት ለፊት እከራከረዋለሁ።
16
ኀጢአተኛ በእርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፣ ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል።
17
ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤ እኔ የምለውንም ጆሯችሁ በሚገባ ይስማ፤
18
እንግዲህ ጕዳዬን ይዤ ቀርቤአለሁ፤ እንደሚፈርድልኝም ዐውቃለሁ።
19
ሊከስሰኝ የሚችል አለ? ካለም፣ ዝም ብዬ ሞቴን እጠብቃለሁ።
20
“አምላክ ሆይ እነዚህን ሁለት ነገሮች ብቻ ስጠኝ፣ ያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፤
21
እጅህን ከእኔ ላይ አንሣ፤ በግርማህም አታስፈራራኝ፤
22
ከዚያ በኋላ ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ ወይም እኔ ልናገር፤ አንተ መልስልኝ።
23
በደሌና ኀጢአቴ ምን ያህል ነው? መተላለፌንና ኀጢአቴን አስታውቀኝ።
24
ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? እንደ ጠላትህስ ለምን ትቈጥረኛለህ?
25
ነፋስ ያረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን? የደረቀውንስ እብቅ ታሳድዳለህን?
26
መራራ ነገር ትጽፍብኛለህ፤ የወጣትነቴንም ኀጢአት ታወርሰኛለህ።
27
እግሬን በእግር ግንድ ታጣብቃለህ፤ ውስጥ እግሬም ላይ ምልክት አድርገህ፣ ዱካዬን አጥብቀህ ትከታተላለህ።
28
“እንደ በሰበሰ ግንድ፣ ብል እንደ በላው ልብስ፣ ሕይወት እያደር ማለቅ ነው።
← Chapter 12
Chapter 14 →