bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 14
Job 14
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
“ከሴት የተወለደ ሰው፣ ዘመኑ ዐጭርና በመከራ የተሞላ ነው፤
2
እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም።
3
እንደዚህ ባለ ሰው ላይ ዐይንህን ታሳርፋለህን? ለፍርድስ በፊትህ ታቀርበዋለህን?
4
ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹሕን ማን ሊያወጣ ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም!
5
የሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፤ የወራቱንም ብዛት ወስነህ አስቀምጠሃል፤ ሊያልፈው የማይችለውንም ገደብ አኖርህለት።
6
እንግዲህ ዘመኑን እንደ ምንደኛ እስኪፈጽም ድረስ፣ ፊትህን ከእርሱ መልስ፤ ተወው።
7
“ዛፍ እንኳ ቢቈረጥ፣ እንደ ገና ሊያቈጠቍጥ፣ አዳዲስ ቅርንጫፍም ሊያበቅል ተስፋ አለው።
8
ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅ፣ ጕቶው በመሬት ውስጥ ቢበሰብስም፣
9
የውሃ ሽታ ባገኘ ጊዜ ያቈጠቍጣል፤ እንደ ተተከለም ችግኝ ቅርንጫፍ ያወጣል።
10
ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?
11
ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣ የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣
12
እንደዚሁም ሰው ይተኛል፤ ቀናም አይልም፤ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም።
13
“ምነው መቃብር ውስጥ በሰወርኸኝ! ቍጣህም እስከሚያልፍ በሸሸግኸኝ! ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!
14
ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል? እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ።
15
ትጠራኛለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ።
16
በዚያን ጊዜ በርግጥ ርምጃዬን ትከታተላለህ፤ ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም።
17
መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።
18
“ተራራ እንደሚሸረሸርና እንደሚወድቅ፣ ዐለትም ከስፍራው እንደሚወገድ፣
19
ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ ጐርፍም ዐፈርን ዐጥቦ እንደሚወስድ፣ አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ።
20
አንድ ጊዜ ፈጽመህ ትበረታለህ፤ እርሱም ያልፋል፤ ገጽታውን ትቀይራለህ፤ ትሸኘዋለህም።
21
ልጆቹ ቢከበሩ አያውቅም፤ ቢዋረዱም አያይም።
22
የገዛ አካሉ ሕመም ብቻ ይሰማዋል፤ ለራሱም ብቻ ያለቅሳል።”
← Chapter 13
Chapter 15 →