bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Samuel 23
2 Samuel 23
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤ “በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣ የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤
2
“ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።
3
የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤ ‘ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣ በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣
4
እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣ እንዳለው ብርሃን ነው፤ በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’
5
“የእኔስ ቤት በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክል አይደለምን? ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን? ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን?
6
ነገር ግን ክፉ ሰዎች ሁሉ፣ በእጅ እንደማይሰበሰብ እንደ እሾኽ ይጣላሉ።
7
እሾኽ የሚነካ ሁሉ፣ የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ ባሉበትም ቦታ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።”
8
የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሴብ በሴትቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው።
9
ከእርሱ ቀጥሎ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ ኤልዔዘር ነበረ፤ እርሱም ለጦርነት አንድ ላይ ተሰብስበው የነበሩትን ፍልስጥኤማውያንን በተገዳደሩ ጊዜ፣ ከዳዊት ጋር ከነበሩት ከሦስቱ ኀያላን ሰዎች አንዱ ነበር። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ሸሹ።
10
እርሱ ግን የቆመበትን ስፍራ አልለቀቀም፤ እጁ እስኪዝልና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ታላቅ ድልን ሰጠ። የሸሸውም ሰራዊት ወደ ኤልዔዘር የተመለሰው የተገደሉትን ሰዎች ለመግፈፍ ብቻ ነበር።
11
ከእርሱም ቀጥሎ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፤ ፍልስጥኤማውያንም ሌሒ በተባለ ስፍራ ምስር በሞላበት አንድ ዕርሻ ላይ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ፣ የእስራኤል ሰራዊት ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤
12
ሣማ ግን የቆመበትን ስፍራ አልለቀቀም፤ ጦርነቱንም ተቋቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ፤ በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ታላቅ ድል ሰጠ።
13
በመከር ወራት፣ የፍልስጥኤም ሰራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ።
14
በዚያም ጊዜ ዳዊት በምሽግ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሰራዊት በቤተ ልሔም ነበረ፤
15
ዳዊትም በናፍቆት፣ “በቤተ ልሔም በር አጠገብ ካለችው ጕድጓድ ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።
16
ስለዚህ ሦስቱ ኀያላን በፍልስጥኤማውያን ሰራዊት መካከል ሰንጥቀው በማለፍ፣ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ካለችው ጕድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን አልጠጣውም፤ ይልቁን በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት አድርጎ አፈሰሰው፤
17
“እርሱም፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላደርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” አለ፤ ዳዊትም ሊጠጣው አልፈለገም። እንግዲህ ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር።
18
የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ እርሱም ዝናን ያተረፈ ሰው ነበረ።
19
አቢሳ ከሦስቱ ይልቅ እጅግ የከበረ አልነበረምን? ከእነርሱ እንደ አንዱ ባይሆንም አለቃቸው ነበረ።
20
የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ እርሱም ሁለት በጣም የታወቁ የሞዓብ ሰዎችን ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጕድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሏል፤
21
ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብፃዊ ገድሏል፤ ግብፃዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም፣ በናያስ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ወደ እርሱ ሄደ፤ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን በመንጠቅ በገዛ ጦሩ ገደለው።
22
የዮዳሄ ልጅ የበናያስ ጀግንነት እንደዚህ ያለ ነበረ፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣
23
ከሠላሳዎቹ ሁሉ በላይ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።
24
ከሠላሳዎቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣
25
አሮዳዊው ሣማ፣ አሮዳዊው ኤሊቃ፣
26
ፈሊጣዊው ሴሌስ፣ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣
27
ዓናቶታዊው አቢዔዜር፤ ኩሳታዊው ምቡናይ ፣
28
አሆሃዊው ጸልሞን፣ ነጦፋዊው ማህራይ፣
29
የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ ፣ ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣
30
ጲርዓቶናዊው በናያስ፣ የገዓስ ሸለቆ ሰው ሂዳይ ፣
31
ዐረባዊው አቢዓልቦን፣ በርሑማዊው ዓዝሞት፣
32
ሸዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣ የአሳን ልጆች፤ ዮናታን የተባለው፣
33
የአሮዳዊው የሣማ ልጅ ፣ የአሮዳዊው የሻራር ልጅ አሒአም፤
34
የማዕካታዊው የአሐሰባይ ልጅ ኤሌፋላት፣ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊአም፣
35
ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፤ አርባዊው ፈዓራይ፣
36
የሱባ ሰው የሆነው የናታን ልጅ ይግዓል፣
37
አሞናዊው ጻሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጦር መሣሪያ ያዥ የነበረው ብኤሮታዊው ነሃራይ፣
38
ይትራዊው ዒራስ፣ ይትራዊው ጋሬብ፣
39
እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ። በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ።
← Chapter 22
Chapter 24 →