bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Samuel 22
2 Samuel 22
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤
2
እንዲህም አለ፤ “ እግዚአብሔር ዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤
3
አምላኬ፣ የምጠጋበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው። እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ ከኀይለኞች ሰዎች ታድነኛለህ።
4
ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
5
“የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ የጥፋትም ጐርፍ አሰጠመኝ።
6
የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ።
7
በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።
8
ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ራዱ።
9
ከአፍንጫው የቍጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ።
10
ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።
11
በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ።
12
ጨለማው በዙሪያው እንዲከበው፣ ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።
13
በእርሱ ፊት ካለው ብርሃን፣ የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።
14
እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።
15
ፍላጻውን ሰድዶ ጠላቶቹን በተናቸው፤ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።
16
ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫው ከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣ የባሕር ሸለቆዎች ታዩ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።
17
“ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ።
18
ከብርቱ ጠላቶቼ፣ ከማልቋቋማቸውም ባላጋሮቼ ታደገኝ።
19
በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፈኝ።
20
ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤ በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።
21
“ እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤ እንደ እጄም ንጹሕነት ብድራትን ከፈለኝ፤
22
የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ ከአምላኬም ዘወር ብዬ ክፉ ነገር አላደረግሁም።
23
ሕጉ ሁሉ በፊቴ ነው፤ ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም።
24
በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤ ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።
25
እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣ በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ።
26
“ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ መሆንህን፣ ለቅን ሰው አንተም ቅን መሆንህን ታሳያለህ።
27
ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።
28
አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤ ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል።
29
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።
30
በአንተ ርዳታ በጠላት ሰራዊት ላይ ወደ ፊት ገፍቼ እሄዳለሁ ፤ በአምላኬም ኀይል ቅጥሩን እዘላለሁ።
31
“የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤ ለሚታመኑበትም ሁሉ ጋሻ ነው፤
32
ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን አለና፤ ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው?
33
ኀይልን የሚያስታጥቀኝ ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው።
34
እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች ያበረታል፤ በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል።
35
እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት ይገትራሉ።
36
የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል።
37
ርምጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተሰነካከሉም።
38
“ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤ እስኪደመሰሱም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም።
39
ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።
40
ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣ ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከክሃቸው።
41
ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው። ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው።
42
ለርዳታ ጮኹ፤ ያዳናቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም።
43
በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አድቅቄ ፈጨኋቸው፤ በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም።
44
“በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ። የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤
45
ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል።
46
ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ ።
47
“ እግዚአብሔር ሕያው ነው፤ ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤ የድነቴ ዐለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።
48
የሚበቀልልኝ አምላክ፣ መንግሥታትንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤
49
እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል። አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።
50
ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም ምስጋና እዘምራለሁ።
51
“ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣ ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል።”
← Chapter 21
Chapter 23 →