bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Chronicles 11
2 Chronicles 11
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ እስራኤልን ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም እንዲመልሱ ከይሁዳና ከብንያም ቤት አንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ወታደሮች ሰበሰበ።
2
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤
3
“ለይሁዳ ንጉሥ ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓምና በይሁዳና በብንያም ላሉ እስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ በል፤
4
‘ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ስለሆነ፣ ወንድሞቻችሁን ለመውጋት ወደዚያ አትውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ’ ” አላቸው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ በኢዮርብዓም ላይ መዝመቱን ትተው ተመለሱ።
5
ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም በማድረግ ለመከላከያ የሚሆኑ ከተሞችን በይሁዳ ሠራ፤ እነዚህም
6
ቤተ ልሔም፣ ኤጣም፣ ቴቁሔ፣
7
ቤትጹር፣ ሦኮ፣ ዓዶላም፣
8
ጌት፣ መሪሳ፣ ዚፍ፣
9
አዶራይም፣ ለኪሶ፣ ዓዜቃ፣
10
ጾርዓ፣ ኤሎን፣ ኬብሮን ናቸው። በይሁዳና በብንያም ውስጥ የተመሸጉት ከተሞች እነዚህ ነበሩ።
11
እነዚህንም ምሽጎቻቸውን አጠንክሮ፣ አዛዦችን ሾመባቸው፤ ምግብ፣ ዘይትና የወይን ጠጅ አከማቸባቸው።
12
በየከተሞቹም ሁሉ ጋሻና ጦር አከማችቶ ይበልጥ አጠናከራቸው። በዚህ ዐይነት ይሁዳንና ብንያምን የራሱ አደረገ።
13
በመላው እስራኤል ያሉት ካህናትና ሌዋውያን ከየክልላቸው ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።
14
ኢዮርብዓምና ልጆቹ ሌዋውያኑን ከእግዚአብሔር የክህነት አገልግሎት ስላባረሯቸው ሌዋውያኑ ማሰማሪያ ቦታቸውንና ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤
15
እርሱም ለየኰረብታው መስገጃ እንዲሁም ለሠራቸው የፍየልና የጥጃ ምስሎች የራሱን ካህናት ሾመ።
16
ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ ከልባቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ።
17
በዚሁ ሁኔታ የዳዊትንና የሰሎሞንን መንገድ በመከተል፣ ለሦስት ዓመት የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምንም ረዱ።
18
ሮብዓም መሐላትን አገባ፤ አባቷ የዳዊት ልጅ ኢያሪሙት ሲሆን፣ እናቷም አቢካኢል የተባለች፣ የእሴይ የልጅ ልጅ የኤልያብ ልጅ ነበረች።
19
እርሷም የዑስ፣ ሰማርያና ዛሃም የተባሉ ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
20
ከዚያም የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን አገባ፤ እርሷም አብያ፣ ዓታይ፣ ዚዛ፣ ሰሎሚት የተባሉትን ወለደችለት።
21
ሮብዓም መዓካን ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይልቅ አብልጦ ወደዳት። በአጠቃላይ ዐሥራ ስምንት ሚስትና ስልሣ ቁባት፣ ሃያ ስምንት ወንድና ስድሳ ሴት ልጆች ነበሩት።
22
ሮብዓም የመዓካን ልጅ አብያን ሊያነግሠው ስለ ፈለገ ከልዑላን ወንድሞቹ ዐልቆ ዋና አደረገው።
23
ከወንዶች ልጆቹም ጥቂቱን በይሁዳና በብንያም አውራጃዎች እንዲሁም በተመሸጉት ከተሞች ስለ ሾማቸው፣ ዘዴኛነቱን አሳይቷል። የሚያስፈልጋቸውን በብዛት ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችም አጋባቸው።
← Chapter 10
Chapter 12 →