bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Chronicles 10
2 Chronicles 10
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እስራኤላውያን ሁሉ ሊያነግሡት ወደዚያ ሄደው ስለ ነበር፣ ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ።
2
ከንጉሥ ሰሎሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ሲሰማ፣ ከግብፅ ተመልሶ መጣ።
3
እርሱንም ልከው አስጠሩት፤ ከዚያም እርሱና እስራኤል ሁሉ ወደ ሮብዓም ሄደው እንዲህ አሉት፤
4
“አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን አስጨናቂውን ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን።”
5
ሮብዓምም፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው፤ ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ።
6
ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም፣ “ለዚህ ሕዝብ ምን እንድመልስለት ትመክሩኛላችሁ?” በማለት አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ ያገለገሉትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠየቃቸው።
7
እነርሱም፣ “ለዚህ ሕዝብ ደግ ከሆንህለት፣ ደስ ካሰኘኸውና የሚስማማው መልስ ከሰጠኸው ምንጊዜም ይገዛልሃል” አሉት።
8
ሮብዓም ግን ሽማግሌዎች የሰጡትን ምክር ትቶ፣ አብሮ አደጎቹና አገልጋዮቹ ከሆኑት ወጣቶች ምክር ጠየቀ፤
9
እንዲህም አላቸው፤ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች የምትሰጡኝ ምክር ምንድን ነው? ምንስ ብለን እንመልስላቸው?”
10
አብሮ አደጎቹም ወጣቶች እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ለጠየቍህ ሕዝብ፤ ‘አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚሉህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤
11
አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ”
12
ንጉሡ፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ሮብዓም ተመለሱ።
13
ንጉሡም የሽማግሌዎችን ምክር በመናቅ፣ አመናጭቆ መለሰላቸው፤
14
እርሱም የወጣቶቹን ምክር በመቀበል፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።
15
እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ወስኖ ስለ ነበር፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።
16
መላው እስራኤልም ንጉሡ ሊሰማቸው አለመፈለጉን በተረዱ ጊዜ፣ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይስ ልጅ ምን ክፍል አለን? እስራኤል፣ ሆይ፤ ወደ ድንኳንህ ተመለስ፤ ዳዊት ሆይ፤ አንተም የገዛ ቤትህን ጠብቅ።” ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ወደየቤታቸው ተመለሱ።
17
ይሁን እንጂ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩትን እስራኤላውያን አሁንም የሚገዛቸው ሮብዓም ነበር።
18
ንጉሥ ሮብዓም የገባሮች ኀላፊ የነበረውን አዶራምን ላከው፤ እስራኤላውያን ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሰረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሽቶ አመለጠ።
19
ስለዚህ እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንደ ዐመፀ ነው።
← Chapter 9
Chapter 11 →