bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 76
Psalms 76
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
2
እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።
3
ድንኳኑ በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው።
4
በዚያም የሚያንጸባርቁ ፍላጻዎችን፥ ጋሻን ሰይፍን ሰልፍንም ሰበረ፥
5
አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ።
6
ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥ እንቅልፋቸውንም አንቀላፉ፥ የጦር ሰዎች በሙሉ በእጃቸው ምንም ማድረግ አልቻሉም።
7
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።
8
አንተ ግን፥ አንተ ግሩም ነህ፥ ቁጣህን ማን ይቃወማል?
9
ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፥ ምድር ፈራች ዝምም አለች፥
10
የምድር ትሑታንን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።
11
የሰውም ቁጣ ሳይቀር ክብርህን ይገልጣል፥ ከዚህ የሚተርፈውንም ትታጠቀዋለህ።
12
ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ፥ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ለሚያስፈራው እጅ መንሻን ያስገቡ።
13
የመኳንንትን ነፍስ ያወጣል፥ በምድርም ነገሥታት ዘንድ ያስፈራል።
← Chapter 75
Chapter 77 →