bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 77
Psalms 77
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር።
2
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ።
3
በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት፥ እጆቼ በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ አላረፍሁምም፥ ነፍሴም መጽናናትን አልቻለችም።
4
እግዚአብሔርን ሳስታውስ እተክዛለሁ ፥ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች።
5
ዐይኖቼ እንዲተጉ ያዝሃቸው፥ ስለተረበሽኩ አልተናገርሁም።
6
የዱሮውን ዘመን አሰብሁ፥ የጥንቱን ዓመታት አሰብሁ፥
7
በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ ነፍሴንም አነቃቃኋት።
8
ጌታ ለዘለዓለም ይጥላልን? እንግዲህስ ቸርነቱን አይጨምርምን?
9
ለዘለዓለምስ ርኅራኄው ተቈረጠችን? የሰጠውስ ቃል ኪዳን ለዘመናት አልቆአልን?
10
እግዚአብሔርስ ማዘኑን ረሳን? በቁጣውስ ርኅራኄውን ዘጋውን?
11
ይህ ድካሜ ነው አልሁ፥ የልዑል ቀኝ መለወጡ።
12
የጌታን ሥራ አስታወስሁ፥ የቀደመውን ተኣምራትህን አስታወሳለሁና፥
13
በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ ሥራህንም አሰላስላለሁ።
14
አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?
15
ተኣምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ። ለሕዝብህ ኃይልህን አስታወቅሃቸው።
16
የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥ ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው።
17
አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆችም አይተውህ ፈሩ፥ ጥልቆችም ተነዋወጡ።
18
ደመኖች ውሃን አዘነቡ፥ ደመኖች ድምፅን ሰጡ፥ ፍላጾችህም በየአቅጣጫው ወጡ።
19
የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነበረ፥ መብረቆች ለዓለም አበሩ፥ ምድር ተናወጠች ተንቀጠቀጠችም።
20
መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥ ያለፍከውም ኃይለኛ ውኆች በኩል ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።
21
በሙሴና በአሮን እጅ ሕዝብህን እንደ በጎች መራሃቸው።
← Chapter 76
Chapter 78 →