bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 75
Psalms 75
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
2
አቤቱ፥ እናመሰግንሃለን እናመሰግንሃለን፥ ስምህም ቅርብ ነው፥ ተኣምራትህን ሁሉ እንናገራለን።
3
“በወሰንኩት ጊዜ እኔ በቅን እፈርዳለሁ።”
4
ምድርና በእርሷ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ይናወጣሉ፥ እኔም ምሰሶችዋን አጠናሁ።
5
ትምክህተኞችን፦ “አትኩሩ፥ ክፉዎችንም፦ ቀንዳችሁን አታንሡ ፥” አልኋቸው
6
ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ፥ በእብሪተኛ አንገት አትናገሩ።
7
ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረበዳ የለምና፥
8
እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህንን ያዋርዳል ያንንም ያከብራል።
9
ጽዋ በጌታ እጅ ነውና፥ ኃይለኛ የወይን ጠጅ ሞላበት፥ ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፥ የምድር ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል።
10
እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል፥ ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬን አቀርባለሁ።
11
“የክፉዎችን ቀንዶች ሁሉ እሰብራለሁ፥ የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።”
← Chapter 74
Chapter 76 →