bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 48
Psalms 48
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
በሁለተኛ ሰንበት የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።
2
ጌታ ትልቅ ነው፥ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።
3
በሰሜን በኩል በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው፥ እርሷም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነች።
4
እግዚአብሔር በአዳራሾችዋ መጠጊያ ሆኖ ይታወቃል።
5
እነሆ፥ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል።
6
እነርሱስ አይተው ተደነቁ፥ ደነገጡ፥ ሸሹም።
7
በዚያ እንደ ወላድ ምጥ መንቀጥቀጥ ያዛቸው።
8
በኃይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ።
9
እንደ ሰማን እንዲሁ አየን በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፥ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል።
10
አምላክ ሆይ፥ በመቅደስህ ውሰጥ ርኅራኄህን አሰላሰልን።
11
አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ ምስጋናህም እንዲሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው፥ ቀኝህ ጽድቅን የተሞላች ናት።
12
አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ።
13
ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቁጠሩ፥
14
በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።
15
ለዓለምና ለዘለዓለም ይህ አምላካችን ነው፥ እርሱም ለዘለዓለም ይመራናል።
← Chapter 47
Chapter 49 →