bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 47
Psalms 47
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2
አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
3
ጌታ ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።
4
አሕዛብን ከእኛ በታች፥ ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን።
5
ለሚወደው ለያዕቆብ ኩራት የሆነችውን ርስታችንን እርሱ ይመርጥልናል።
6
አምላክ በእልልታ፥ ጌታ በመለከት ድምፅ ዐረገ።
7
ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፥ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
8
እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፥ በጥበብ ዘምሩ።
9
እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፥ እግዚአብሔር በተቀደሰው ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
10
የአሕዛብ አለቆች፥ እንደ አብርሃም አምላክ ሕዝብ ተሰበሰቡ፥ የምድር ጋሻዎች የእግዚአብሔር ናቸውና፤ እርሱም እጅጉን ከፍ ብሏል።
← Chapter 46
Chapter 48 →