bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 49
Psalms 49
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2
አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፥ በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ፥
3
ዝቅተኞችና ከፍተኞች፥ ሀብታሞችና ድሆች በአንድነት።
4
አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አስተንትኖ ማስተዋልን።
5
ጆሮዬን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።
6
በደል ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
7
በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በሀብታቸውም ብዛት የሚመኩ፥
8
በእውነት ማንም እራሱን አያድንም፥ ማንም ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥
9
የነፍሳቸው ዋጋ ክቡር ነው፥ መቼውንም በቂ አይሆንም፥
10
ሰው ገና እንዲኖርና አዘቅቱንም እንዳያይ
11
ጠቢባን እንደሚሞቱ፥ ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንደሚጠፉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንደሚተዉ አይቶአል።
12
ብዙ መሬት በስማችው ቢያስጠሩም እንኳን፥ መቃብራቸው የዘለዓለም ቤታቸው፥ ለልጅ ልጅ የሚሆን ማደሪያቸውም ነው።
13
ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፥ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።
14
ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በንግግራቸው ይደሰታሉ።
15
እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥ እረኛቸውም ሞት ነው፥ ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች።
16
ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።
17
የሰው ሀብት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥
18
በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥ ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና።
19
በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና ለሰውነቱ መልካም በማድረጉ ይወደሳልና።
20
ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፥ ለዘለዓለም ብርሃንን ወደ ማያዩበት።
21
አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።
← Chapter 48
Chapter 50 →