bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 141
Psalms 141
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ በፍጥነት ድረስልኝ፥ ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ድምፅ ስማ።
2
ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን፥ እጆቼን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይሁን።
3
አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
4
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለክፋት ምክንያት እንዳልሰጥ፥ ከድግሳቸውም አልቅመስ።
5
ጻድቅ በጽኑ ፍቅር ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የክፉ ሰው ዘይት ግን ራሴን አይቀባ፥ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና።
6
አለቆቻቸው በዓለት አጠገብ ተጣሉ፥ ጣፋጭ ናትና ቃሌን ይሰማሉ።
7
በምድር ላይ እንደ ተሰነጠቀ እንደ መሬት ጓል፥ እንዲሁ አጥንቶቻችን በሲኦል ተበተኑ።
8
አቤቱ ጌታ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፥ በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አትተዋት።
9
ከሰወሩብኝ ወጥመድ፥ ዓመፅንም ከሚያደርጉ ሰዎች ዕንቅፋት ጠብቀኝ።
10
እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ክፉዎች በወጥመዳቸው ይውደቁ።
← Chapter 140
Chapter 142 →