bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 140
Psalms 140
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2
አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥ ከዓመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ
3
በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥ ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።
4
ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፥ ከከንፈራቸው በታች የእፉኝት መርዝ አለ።
5
አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥ እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዓመፀኞች አድነኝ።
6
ትዕቢተኞች ወጥመድን ሰወሩብኝ፥ ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ፥ በመንገድ ዕንቅፋትን አኖሩ።
7
ጌታንም፦ አንተ አምላኬ ነህ፥ የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ አልሁት።
8
አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጉልበት፥ በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ።
9
አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥ ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።
10
የሚከብቡኝ ራሳቸውን አነሡ ፥ የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው።
11
የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፥ እንዳይነሡም ወደ እሳትና ወደ አዘቅት ይጣሉ።
12
ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፥ ዓመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል።
13
ጌታ ለድሀ ዳኝነትን ለችግረኛም ፍርድን እንደሚያደርግ አወቅሁ።
14
ጻድቃንም በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ፥ ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።
← Chapter 139
Chapter 141 →