bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 142
Psalms 142
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ጸሎት፥ በዋሻ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት ትምህርት።
2
በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ለመንሁ።
3
ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥ መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።
4
መንፈሴ በዛለ ጊዜ መንገዴን አወቅሁ፥ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
5
ወደ ቀኝ ተመለከትሁ አየሁም፥ የሚያውቀኝም አጣሁ፥ መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ነፍሴም የሚያስብ የለም።
6
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ በሕያዋንም ምድር አንተ እድል ፈንታዬ ነህ አልሁ።
7
እጅግ ተቸግሬአለሁና ጩኸቴን አድምጥ፥ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
8
አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፥ ስለ ምታጠግበኝ ጻድቃን እኔን ይከባሉ።
← Chapter 141
Chapter 143 →