bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 97
Psalms 97
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፥ የእግዚአብሔር ሥራ፥ የቀኙ ማዳን፥ የተቀደሰ ክንዱም ድንቅ ነውና።
2
እግዚአብሔር ማዳኑን አሳየ። በአሕዛብም ፊት ቃል ኪዳኑን ገለጠ።
3
ለያዕቆብ ይቅርታውን ለእስራኤልም ቤት እውነቱን አሰበ፤ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ፥ የአምላካችንን ማዳን እዩ።
4
በምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ አመስግኑ፥ ደስም ይበላችሁ፥ ዘምሩም።
5
ለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።
6
በነጋሪትና በመለከት ድምፅ፥ በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።
7
ባሕር በሞላዋ፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ይናወጡ።
8
ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥
9
ለምድር በዚያ ይፈረድላታልና። ለዓለምም በእውነት ይፈረድላታልና። ለአሕዛብም በቅንነት ይፈረዳል።
← Chapter 96
Chapter 98 →