bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 98
Psalms 98
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ደነገጡ፤ በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ፥ ምድርን አነዋወጣት።
2
እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
3
ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመሰግናል፥ ግሩምና ቅዱስ ነውና።
4
ክቡር ንጉሥ ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ በኀይልህ ጽድቅን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።
5
ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ ከእግሩ መረገጫ በታችም ይሰግዱለታል።
6
ሙሴና አሮን በክህነታቸው ቅዱሳን ናቸውና ሳሙኤልም ስሙን ከሚጠሩት ጋራ፤ እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።
7
በደመና ዐምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።
8
አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ በሥራቸው ሁሉ ግን ትበቀላቸዋለህ።
9
አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
← Chapter 97
Chapter 99 →