bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 96
Psalms 96
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር ነገሠ፥ ምድር ሐሤትን ታደርጋለች፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይላቸዋል።
2
ደመናና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤ ፍትሕና ርትዕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው፤
3
እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ነበልባሉም ጠላቶቹን ይከብባቸዋል።
4
መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፤ ምድር ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም።
5
ተራሮችም ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ እንደ ሰም ቀለጡ፥ ምድር ሁሉ ከአግዚአብሔር ፊት የተነሣ ቀለጠች።
6
ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።
7
ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱም ሁሉ ይሰግዱለታል።
8
አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት አደረጉ፤
9
አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ብቻህን ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።
10
እግዚአብሔርን የምትወድዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የጻድቃኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።
11
ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።
12
ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይላቸዋል። ለቅድስናውም መታሰቢያ ያመሰግናሉ።
← Chapter 95
Chapter 97 →