bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 93
Psalms 93
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው።
2
የምድር ፈራጅ፥ ከፍ ከፍ አለ፤ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።
3
አቤቱ፥ ኃጥኣን እስከ መቼ? ኃጥኣን እስከ መቼ ይታበያሉ?
4
ይከራከራሉ፥ ዐመፃንም ይናገራሉ፤ ዐመፃንም የሚያደርጉ ሁሉ ይናገራሉ።
5
አቤቱ፥ ሕዝብህን አዋረዱ፥ ርስትህንም አሠቃዩ።
6
ባልቴቲቱንና ድሃ አደጉን ገደሉ፥ ስደተኛውንም ገደሉ።
7
“እግዚአብሔር አያይም፥ የያዕቆብም አምላክ አያውቅም” አሉ።
8
ሰነፎች ሕዝብ ሆይ፥ ልብ አድርጉ፤ ሰነፎችም መቼ ይጠበባሉ?
9
ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዐይንን የሠራው አያይምን?
10
አሕዛብንስ የሚገሥጸው፥ ለሰዎችም ዕውቀትን የሚያስተምረው እርሱ አይዘልፍምን?
11
የጠቢባን ዐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ያውቃል።
12
አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።
13
ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ ለኃጥኣን ጕድጓድ እስኪቆፈር ድረስ።
14
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውምና፥ ርስቱንም አይተዋቸውምና
15
ፍርድ ለእውነተኛ እስኪመለስ ድረስ፥ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።
16
ስለ ክፉዎች ማን ይከራከርልኛል? ዐመፃንስ ስለሚያደርጉ ማን ይቆምልኛል?
17
እግዚአብሔር የረዳኝ ባይሆን ነፍሴ ለጥቂት ጊዜ በሲኦል ባደረች ነበር።
18
እግሮች ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ምሕረትህ ረዳኝ።
19
አቤቱ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት፥ ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
20
በሕግ ላይ ድካምን የሚፈጥር፥ የዐመፃ ዙፋን አይቃወምህም፥
21
የጻድቅን ነፍስ ያድናታል፥ በንጹሕ ደምም ይፈርዳል።
22
እግዚአብሔር መጠጊያዬ ሆነኝ፥ አምላኬ የተስፋዬም ረዳት ነው።
23
እግዚአብሔርም እንደ ክፋታቸው ፍዳቸውን ይከፍላቸዋል፥ አምላካችን እግዚአብሔርም ያጠፋቸዋል።
← Chapter 92
Chapter 94 →