bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 94
Psalms 94
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን፤ ለአምላካችንና ለመድኀኒታችንም እልል እንበል፥
2
በእምነት ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፤
3
አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።
4
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውምና፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ በእጁ ውስጥ ናቸውና፥ ረዣዥም ተራሮች የእርሱ ናቸውና።
5
ባሕር የእርሱ ናትና፥ እርሱም ፈጥሯታልና። የብስንም በእጁ ፈጥሯታልና።
6
ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ በፈጠረን በእግዚአብሔር ፊት እናልቅስ፤
7
እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ ግን ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።
8
በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑትና እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ።
9
የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ፈተኑኝ፥ ሥራዬንም አዩ።
10
“ይችን ትውልድ አርባ ዓመታት ተቈጥቻት ነበር፥ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም” አልሁ።
11
ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቍጣዬ ማልሁ።
← Chapter 93
Chapter 95 →