bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 92
Psalms 92
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብሩንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኀይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምንም እንዳትናወጥ አጸናት።
2
አቤቱ፥ ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም መቼም መች እስከ ዘለዓለም ነህ።
3
አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ።
4
ከብዙ ውኆች ድምፅ የተነሣ የባሕር እንቅስቃሴዋ ድንቅ ነው። ድንቅስ በልዕልና የሚኖር እግዚአብሔር ነው።
5
ምስክርህ እጅግ የታመነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤትህ ምስጋና ይገባል።
← Chapter 91
Chapter 93 →