bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 91
Psalms 91
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም መዘመር፤
2
በማለዳ ምሕረትህን፥ በሌሊትም እውነትህን መናገር፥
3
ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
4
አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፤ በእጆችህም ሥራ ደስ ይለኛልና።
5
አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳብህም እጅግ ጥልቅ ነው።
6
ሰነፍ ሰው አያውቅም፥ ልብ የሌለውም ይህን አያስተውለውም።
7
ኃጥኣን እንደ ሣር በበቀሉ ጊዜ፥ ዐመፃን የሚያደርጉም ሁሉ በለመለሙ ጊዜ፥ ለዘለዓለም ዓለም እንደሚጠፉ ነው።
8
አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፤
9
አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥ ዐመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና።
10
ቀንዴ አንድ ቀንድ እንዳለው ከፍ ከፍ ይላል፥ ሽምግልናዬም በዘይት ይለመልማል።
11
ዐይኔም በጠላቶቼ ላይ አየች፥ ጆሮዬም በእኔ ላይ በቆሙ በክፉዎች ላይ ሰማች።
12
ጻድቅ ግን እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይበዛል፥
13
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተተከሉ ናቸው፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
14
ያንጊዜ በመልካም ሽምግልና ይበዛሉ፤ ዕረፍት ያላቸውም ሆነው ይኖራሉ።
15
አምላካችን እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ ይናገራሉ፥ በእርሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።
← Chapter 90
Chapter 92 →