bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 90
Psalms 90
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በልዑል ረድኤት የሚያድር፥ በሰማይ አምላክ ጥላ ውስጥ የሚቀመጥ፥
2
እግዚአብሔርን፥ “አንተ መጠጊያዬና አምባዬ ነህ፤ አምላኬና ረዳቴ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ” ይለዋል።
3
እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፥ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድነኛልና።
4
በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
5
ከሌሊት ግርማ፥ በመዓልት ከሚበርር ፍላጻ፥
6
በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ሥራ፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
7
በአጠገብህ ሺህ፥ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርቡም።
8
በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ፍዳ ታያለህ።
9
አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
10
ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
11
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
12
እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
13
በተኵላና በእባብ ላይ ትጫናለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
14
በእኔ ተማምኖአልና አድነዋለሁ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
15
ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
16
ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
← Chapter 89
Chapter 91 →