bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 89
Psalms 89
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ አንተ ለልጅ ልጅ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።
2
ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።
3
ሰውን ወደ ኀሣር አትመልሰው፤ የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመለሱ ትላለህ፤
4
ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ሰዓት ነውና።
5
ዘመኖች በፊትህ የተናቁ ናቸው፥ በማለዳም እንደ ሣር ያልፋል።
6
ማልዶ ይበቅላል ያልፋልም፥ በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።
7
እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመቅሠፍትህም ደንግጠናልና።
8
ኀጢአታችንን በፊትህ አስቀመጥህ፥ ዓለማችንም በፊትህ ብርሃን ነው።
9
ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመቅሠፍትህ አልቀናልና፤ ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይሆናሉ።
10
የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥ ቢበዛም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ከእነዚህ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ የዋህነት ከእኛ አልፋለችና፥ እኛም ተገሥጸናልና።
11
የመቅሠፍትህን ኀይል ማን ያውቃል? ከቍጣህ ግርማ የተነሣ አለቁ።
12
ጥበብን በልብ ለተማሩ፥ ቀኝህን እንዲህ ግለጥ።
13
አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ስለ ባሪያዎችህም ተሟገት።
14
በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለንና፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።
15
መከራን ባሳየኸን ዘመን ፋንታ፥ ክፉንም ባየንባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለናል።
16
ባሪያዎችህንና ሥራህን እይ፥ ልጆቻቸውንም ምራቸው።
17
የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ ያቃናልናል።
← Chapter 88
Chapter 90 →