bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 84
Psalms 84
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፦ ምድርህን ይቅር አልኽ። የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።
2
የሕዝብህን ኀጢአት ይቅር አልህ፤ ዐበሳቸውንም ሁሉ ሰወርህ።
3
መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፤ ከቍጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።
4
አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ፥ መልሰን፥ ቍጣህንም ከእኛ መልስ።
5
ለዘለዓለም አትቈጣን፥ ቍጣህንም ለልጅ ልጅ አታስረዝም።
6
አንተ አምላካችን ሆይ፥ ተመለስልን፥ አድነንም፤ ሕዝብህም በአንተ ደስ ይላቸዋል።
7
አቤቱ፥ ምሕረትህን አሳየን፥ አቤቱ፥ ማዳንህን ስጠን።
8
እግዚአብሔር አምላኬ የሚናገረኝን አደምጣለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለጻድቃኑ፥ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።
9
ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው።
10
ይቅርታና ቅንነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።
11
ቅንነት ከምድር በቀለች፥ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተ።
12
እግዚአብሔርም ምሕረቱን ይሰጣል፥ ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች።
13
ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፥ ፍለጋውንም በመንገድ ውስጥ ይተዋል።
← Chapter 83
Chapter 85 →