bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 85
Psalms 85
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል ስማኝም፥ ድሃና ምስኪን ነኝና።
2
እኔ የዋህ ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤ አምላኬ ሆይ፥ አንተን የታመነውን ባሪያህን አድነው።
3
አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ይቅር በለኝ።
4
የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።
5
አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ይቅርታህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።
6
አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ቃል ስማ።
7
ትሰማኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ።
8
አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥ እንደ ሥራህም ያለ የለም።
9
የፈጠርሃቸው አሕዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊትህም ይስገዱ፥ ስምህንም ያክብሩ፤
10
አቤቱ፥ ድንቅን የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና፥
11
አቤቱ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህንም ለመፍራት ልቤን ደስ ይለዋል።
12
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ። ለዘለዓለምም ስምህን አከብራለሁ፤
13
ምሕረትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛዪቱ ሲኦል አድነሃታልና።
14
አምላኬ ሆይ፥ ዐመፅኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥ የክፉዎችም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት፤ አንተንም በፊታቸው አላደረጉህም።
15
አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህ፤ መዓትህ የራቀ፥ ምሕረትህም የበዛ፥ እውነተኛም ነህ።
16
ወደ እኔ ተመልከት፥ ይቅር በለኝም፤ ለባሪያህ ኀይልን ስጠው፥ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን።
17
ምልክትንም ለመልካም ከእኛ ጋር አድርግ፤ ጠላቶቻችንም ይዩ፥ ይፈሩም፥ አቤቱ፥ አንተ ረድተኸናልና፥ ደስም አሰኝተኸናልና።
← Chapter 84
Chapter 86 →