bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 83
Psalms 83
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የኀያላን አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እጅግ የተወደዱ ናቸው።
2
አቤቱ፥ ነፍሴ አደባባዮችህን በመውደድ ደስ አላት፤ ልቤም ሥጋዬም በሕያው እግዚአብሔር ደስ አላቸው።
3
ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፤ የኀያላን አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥ እርሱ መሠዊያህ ነው።
4
በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ ብፁዓን ናቸው፤ ለዓለምና ለዘለዓለም ያመስግኑሃል።
5
አቤቱ፥ ርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ብፁዕ ነው።
6
በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰንኻቸው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።
7
ከኀይል ወደ ኀይልም ይሄዳል፥ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።
8
የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጠኝ።
9
አቤቱ፥ መታመኔን እይልኝ፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።
10
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።
11
እግዚአብሔር አምላክ ምጽዋትንና እውነትን ይወድዳልና፥ እግዚአብሔር ክብርና ሞገስን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከበረከቱ አያሳጣቸውም።
12
አቤቱ የኀያላን አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ብፁዕ ነው።
← Chapter 82
Chapter 84 →