bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 75
Psalms 75
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ሆነ።
2
በሀገሩም በሰላም ኖረ፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው፤
3
በዚያም የቀስትን ኀይል፥ ጋሻን፥ ጦርንና ሰልፍንም ሰበረ፤ በዚያም ቀንዶችን ሰበረ።
4
አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ።
5
ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥ ሕልምን አለሙ፥ ያገኙት ግን የለም፤ ሰው ሁሉ ለእጁ ባለጠግነት ነው።
6
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ሁሉ አንቀላፉ።
7
አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤ ቍጣህን ማን ይቃወማል?
8
ፍርድን ከሰማይ ታሰማለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥
9
ልበ የዋሃንን ሁሉ ያድን ዘንድ፥ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።
10
ሰው በፈቃዱ ያመሰግንሃልና፥ ከሕሊናቸው ትርፍም በዓልህን ያደርጋሉ።
11
ለአምላካችን ለአግዚአብሔር ስእለትን ሰጡ፤ በዙሪያውም ያሉ ሁሉ እጅ መንሻን ለሚያስፈራው ያገባሉ።
12
የአለቆችን ነፍስ ያወጣል፤ በምድርም ነገሥታት ዘንድ ያስፈራል።
← Chapter 74
Chapter 76 →