bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 74
Psalms 74
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ አመሰግንሃለሁ፤ አመሰግንሃለሁ ስምህንም እጠራለሁ፤ ተአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።
2
ጊዜውን ባገኘሁ ጊዜ እኔ በቅን እፈርዳለሁ።
3
ምድርና በእርስዋ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰሶዎችዋን አጸናሁ።
4
ኃጥኣንን አልኋቸው፥ “አትበድሉ” የሚበድሉትንም አልኋቸው፥ “ቀንዳችሁን አታንሡ፥
5
ቀንዳችሁን እስከ አርያም አታንሡ፥ በእግዚአብሔር ላይ ዐመፃን አትናገሩ።”
6
ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤
7
እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል።
8
ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና፤ ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት፤ ከዚህ ወደዚህ አቃዳው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፤ የምድር ኃጥኣን ሁሉ ይጠጡታል።
9
እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል፥ ለያዕቆብም አምላክ እዘምራለሁ፥
10
የኃጥኣንን ቀንዶች ሁሉ እሰብራለሁ። የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።
← Chapter 73
Chapter 75 →