bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 76
Psalms 76
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ።
2
በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እጆቼም በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ ጠላቶቼም አልረገጡኝም። ነፍሴ ግን ደስታን አጣች።
3
እግዚአብሔርን ዐሰብሁት፥ ደስ አለኝም፤ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች። የጠላቶቼን ሁሉ ሰዓቶች ዐወቅኋቸው
4
ደነገጥሁ አልተናገርሁምም።
5
የድሮውን ዘመን ዐሰብሁ፤ የዘለዓለሙን ዓመታት ዐሰብሁ፤ አነበብኹም፤
6
በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ መንፈሴንም አነቃቃኋት።
7
እግዚአብሔር ለዘለዓለም በውኑ ይጥላልን? እንግዲህስ ይቅርታውን አይጨምርምን?
8
ለዘለዓለምስ ምሕረቱን ለልጅ ልጅ ይቈርጣልን?
9
እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን?
10
እነሆ፥ ዛሬ ጀመርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እንደሚያፈራርቅ።
11
የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስሁ፤ የቀደመውን ተአምራትህን አስታውሳለሁና፤
12
በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ በሥራህም እጫወታለሁ።
13
አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?
14
ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ለሕዝብህ ኀይልህን አሳየሃቸው።
15
የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥ ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው።
16
አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆች አይተው ፈሩ፤ የውኆች ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆቻቸውም ጮኹ።
17
ደመናት ድምፅን ሰጡ፥ ፍላጾችህም ወጡ።
18
የነጐድጓድህ ድምፅ በሰረገላ ነበረ፤ መብረቆች ለዓለም አበሩ፤ ምድር ተናወጠች፥ ተንቀጠቀጠችም።
19
መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥ ፍለጋህም በብዙ ውኆች ነው፥ ፍለጋህም አይታወቅም።
20
በሙሴና በአሮን እጅ ሕዝብህን እንደ በጎች መራሃቸው።
← Chapter 75
Chapter 77 →