bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 73
Psalms 73
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸን? በማሰማሪያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ለምን ተቈጣህ?
2
አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዠሃትንም የርስትህን በትር፥ በውስጥዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ ዐስብ።
3
ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜ በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።
4
ጠላቶችህ በበዓልህ መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።
5
እንደ ላይኛው መንገድ፥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በገጀሞ በሮችዋን ሰበሩ።
6
እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።
7
መቅደስህንም በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።
8
አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው አሉ፦ “ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓላት ከምድር እንሻር
9
ምልክቱንም አናውቅም፥ ከእንግዲህ ወዲህ ነቢይ የለም፤ እኛም ከእንግዲህ ወዲህ አናውቅም።”
10
አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህንስ ጠላት ሁልጊዜ ያስቈጣዋል?
11
አቤቱ፥ እጅህን ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ? ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥
12
እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ።
13
አንተ ባሕርን በኀይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቡን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
14
አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
15
አንተ ፈሳሾቹንና ምንጮቹን ሰነጠቅህ።
16
ቀኑ የአንተ ነው፥ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሐይንና ጨረቃን ፈጠርህ።
17
አንተ የምድር ዳርቻዎችን ሁሉ ሠራህ፤ በጋንና ክረምትን አንተ አደረግህ።
18
ይህን ፍጥረትህን ዐስብ። ጠላት እግዚአብሔርን ተገዳደረው። ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ።
19
የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት፤ የድሆችህንም ነፍስ ለዘወትር አትርሳ።
20
ወደ ኪዳንህም ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኃጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።
21
ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፤ ድሃና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።
22
አቤቱ፥ ተነሥ፥ በቀሌንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜ የተገዳደሩህን ዐስብ።
23
የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ፤ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይውጣ።
← Chapter 72
Chapter 74 →