bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 72
Psalms 72
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እጅግ ቸር ነው።
2
እኔ ግን እግሮች ሊሰናከሉ፥ አረማመዴም ሊወድቅ ጥቂት ቀረ።
3
የዐመፀኞችን ሰላም አይቼ በኃጥኣን ላይ ቀንቼ ነበርና።
4
ለሞታቸው እረፍት የለውምና፤ ለመቅሠፍታቸውም ኀይል የለውምና፤
5
በድካምም ጠላት አልሆኑም። ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6
ስለዚህም ትዕቢት ያዛቸው፤ ኀጢአታቸውንና በደላቸውን ተጐናጸፉአት።
7
መቅን ከቅልጥም እንደሚወጣ ኀጢአታቸው ይወጣል። ልባቸውም ከትዕቢት አለፈ።
8
ዐስበው ከንቱ ነገርን ተናገሩ። በአርያምም ዐመፃን ተናገሩ።
9
አፋቸውንም በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ላይ ተመላለሰ።
10
ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤
11
“እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በአርያምስ በውኑ የሚያውቅ አለን?” ይላሉ።
12
እነሆ፥ እነዚህ ኃጥኣን ደስ ይላቸዋል፤ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያጸኗታል፤
13
እንዲህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁአትን?” እጆቼንም በንጽሕና አጠብሁ።
14
ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።
15
እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16
አውቅም ዘንድ ተቀበልኸኝ፥ ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው።
17
ፍጻሜአቸውን አውቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥
18
ነገር ግን ስለ ሽንገላቸው አቈየሃቸው፥ በመነሣታቸውም ጣልኻቸው።
19
እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ ስለ ኀጢአታቸውም ጠፉ።
20
ከእንቅልፍ እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ በከተማህ ምልክታቸውን ታስነውራለህ።
21
ልቤ ነድዶአል፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና፤
22
እኔ የተናቅሁ ነኝ፥ አላወቅሁምም፥ በአንተ ዘንድ እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23
እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
24
በአንተ ምክር መራኸኝ፤ በክብርም ተቀበልኸኝ።
25
በሰማይ ያለኝ ምንድን ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ በቀር ምን እሻለሁ?
26
የመድኀኒቴ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ዕድል ፋንታዬ ነው።
27
እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው።
28
ለእኔ ግን እግዚአብሔርን መከተል ይሻለኛል፤ መታመኛዬም በእግዚአብሔር ላይ ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።
← Chapter 71
Chapter 73 →