bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 71
Psalms 71
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጠው፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥
2
ሕዝብህን በጽድቅ፥ ድሆችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።
3
ተራሮችና ኮረብቶች የሕዝብህን ሰላም ይቀበሉ።
4
ለድሆች ሕዝብህ በጽድቅ ፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች አድናቸው። ትዕቢተኛውንም አዋርደው።
5
ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለልጅ ልጅ ይኑር።
6
እንደ ጠል በባዘቶ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል።
7
በዘመኑም ጽድቅ ይበቅላል፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።
8
ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ይገዛል።
9
በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈርን ይልሳሉ።
10
የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የሳባና የዓረብ ነገሥታት እጅ መንሻን ያመጣሉ፤
11
የምድር ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል ፥ አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።
12
ድሃውን ከሚቀማው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።
13
ለድሃና ለምስኪን ይራራል፥ የድሆችንም ነፍስ ያድናል።
14
ከአራጣና ከቅሚያ ነፍሳቸውን ያድናታል፤ ስሙም በፊታቸው ክቡር ነው።
15
እርሱ ይኖራል፥ ከዓረብም ወርቅን ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ስለ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይመርቁታል።
16
በተራሮች ራስ ላይ ለምድር ሁሉ መጠጊያ ይሆናል፤ ፍሬውም ከሊባኖስ ዛፍ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፤ እንደ ምድር ሣር በከተማ ይበቅላል።
17
ስሙ ለዘለዓለም ቡሩክ ነው፥ ከፀሓይም አስቀድሞ ስሙ ነበረ፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ ሕዝቡ ሁሉ ያመሰግኑታል።
18
ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።
19
የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።
← Chapter 70
Chapter 72 →