bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 62
Psalms 62
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ
2
ኀይልህንና ክብርህን ዐውቅ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።
3
ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና፥ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
4
እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆችን አነሣለሁ።
5
ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ደስተኞች ከንፈሮቼም ስምህን ያመሰግናሉ።
6
በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ፤
7
ረዳቴ ሆነኽልኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ እታመናለሁ።
8
ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።
9
እነርሱ ግን ነፍሴን ለከንቱ ፈለጓት፤ ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ።
10
በሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጡ፥ የቀበሮዎችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።
11
ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤ በእርሱም የሚምል ሁሉ ይከብራል፥ ዐመፅን የሚናገር አፍ ይዘጋልና።
← Chapter 61
Chapter 63 →