bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 63
Psalms 63
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ወደ አንተ የለመንሁትን ጸሎቴን ስማኝ፥ ከጠላትም ጥርጥር ነፍሴን አድናት።
2
ከክፉዎች ሴራ ከብዙዎች ዐመፅ አድራጊዎች ሰውረኝ።
3
እንደ እባብ ምላሳቸውን አሰሉ፤ መራራ ነገርን ለማድረግ፥
4
ንጹሕንም በስውር ለመግደል ቀስትን ገተሩ፤ በድንገት ይነድፏቸዋል አይፈሩምም።
5
ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፤ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፤ የሚያምንም የለም ይላሉ።
6
ዐመፃን ፈለጓት፥ ሲፈትኑም ሲጀምሩም አለቁ፤ ሰው በጥልቅ ልብ ውስጥ ይገባል፥
7
እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። መቅሠፍታቸው እንደ ልጆች ሕንፃ ሆነ፤
8
አንደበታቸው በላያቸው ደከመ፥ የሚያዩአቸውም ሁሉ ደነገጡ።
9
ሰው ሁሉ ፈራ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም ዐወቁ።
10
ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል፤ ልባቸውም የቀና ሁሉ ይከብራሉ።
← Chapter 62
Chapter 64 →