bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 61
Psalms 61
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኀኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
2
እርሱ አምላኬ መድኀኒቴም ነውና፤ እርሱ ረዳቴ ነው ሁልጊዜም አልታወክም።
3
እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድሉታላችሁ።
4
ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ በጥሜም ሮጥሁ፤ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።
5
ነገር ግን ነፍሴ፥ ለእግዚአብሔር ትገዛለች፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
6
እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ ረዳቴ ነውና፥ አልታወክም።
7
መድኃኒቴ በእግዚአብሔር ነው፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ነው፥ የረድኤቴ አምላክ፥ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።
8
የአሕዛብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፥ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው።
9
ነገር ግን የሰው ልጆች ሁሉ ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው፤ በሚዛንም ይበድላሉ፥ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው።
10
ዐመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁን አታኩሩ።
11
እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ይቅርታ የእግዚአብሔር ነውና፥
12
አቤቱ፥ ኀይልም ያንተ ነው፤ አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህና።
← Chapter 60
Chapter 62 →