bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 60
Psalms 60
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬን ስማኝ፥ ጸሎቴንም አድምጠኝ።
2
ልቤ ተስፋ በቈረጠ ጊዜ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በድንጋይ ላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ።
3
በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤ ተስፋዬም ሆነኽልኛልና መራኸኝ።
4
በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፤ በክንፎችህ ጥላም እጋረዳለሁ፤
5
አምላኬ፥ አንተ ጸሎቴን ሰምተሃልና፤ ለሚፈሩህም ርስትን ሰጠሃቸው።
6
ለንጉሥ ከቀን በላይ ቀንን ትጨምራለህ፥ ዓመታቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናሉ።
7
በእግዚአብሔርም ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፤ ይቅርታውንና ጽድቁን ማን ይፈልጋል?
8
እንዲሁ ለስምህ ለዘለዓለም እዘምራለሁ ምኞቴን ሁልጊዜ ትሰጠኝ ዘንድ።
← Chapter 59
Chapter 61 →