bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 46
Psalms 46
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለአግዚአብሔር እልል በሉ።
2
እግዚአብሔር ልዑል፥ ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።
3
አሕዛብን ከእኛ በታች፥ ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን።
4
ለርስቱ እኛን መረጠን፥ የያዕቆብን ውበት የወደደ።
5
እግዚአብሔር በእልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዐረገ።
6
ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
7
እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማስተዋል ዘምሩ፤
8
እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፤ እግዚአብሔር በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
9
የአሕዛብ አለቆች ከአብርሃም አምላክ ጋር ተሰበሰቡ፤ የምድር ኀይለኞች ለእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብለዋልና።
← Chapter 45
Chapter 47 →