bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 45
Psalms 45
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ባገኘን በታላቅ መከራም ጊዜ ረዳታችን ነው።
2
ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈልሱ አንፈራም።
3
ውኆቻቸው ጮኹ ደፈረሱም፥ ተራሮችም ከኀይሉ የተነሣ ተናወጡ።
4
ፈሳሽ ወንዝ የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛል፤ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።
5
እንዳትታወክም እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው፥ እግዚአብሔርም ፊት ለፊት ይረዳታል።
6
አሕዛብ ደነገጡ ነገሥታትም ተመለሱ፤ ልዑል ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።
7
የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
8
የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተአምራት እንድታዩ ኑ።
9
ከምድር ዳርቻ ጦርነትን ይሽራል፤ ቀስትን ይሰብራል፥ ጋሻንም ይቀጠቅጣል፥ በእሳትም የጦር መሣሪያን ያቃጥላል።
10
ልብ አድርጉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።
11
የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
← Chapter 44
Chapter 46 →