bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 47
Psalms 47
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በመቅደሱ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።
2
ለምድር ሁሉ ደስታን የሚያዝዝ፥ የጽዮን ተራራዎች በመስዕ በኩል ናቸው። የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናት።
3
በተቀበሏት ጊዜ እግዚአብሔር በረከትዋን ያውቃል
4
እነሆ፥ የምድር ነገሥታት ተሰብስበው በአንድነት መጥተዋል።
5
እነርሱስ ይህን አይተው አደነቁ፥ ደነገጡ፥ ፈሩም።
6
መንቀጥቀጥም ያዛቸው፥ እንደ ወላድም በዚያ አማጡ።
7
በኀይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትቀጠቅጣቸዋለህ።
8
እንደሰማን እንዲሁ አየን፥ በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል።
9
አምላክ ሆይ፥ በአሕዛብ መካከል ይቅርታህን ተቀበልን።
10
አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ እንዲሁም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስጋናህ ነው። ቀኝህ ጽድቅን የተመላ ነው።
11
አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራሮች ደስ ይላቸዋል፥ የይሁዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት ያደርጋሉ።
12
ጽዮንን ክበቡአት፥ ዕቀፉአትም። በቅጥሮችዋም ተናገሩ፤
13
በብርታቷ ልባችሁን አኑሩ፤ በረከቷንም ትካፈላላችሁ ለሚመጣውም ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።
14
ለዓለምና ለዘለዓለም ይህ አምላካችን እንደ ሆነ፥ እርሱም ለዘለዓለም ይጠብቀናል።
← Chapter 46
Chapter 48 →