bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 44
Psalms 44
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ልቤ መልካም ነገርን ተናገረ፥ እኔም ሥራዬን ለንጉሥ እናገራለሁ፤ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።
2
ውበቱ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል፤ ሞገስ ከከንፈሮችህ ፈሰሰ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከህ።
3
ኀያል ሆይ፥ በደም ግባትህና በውበትህ፥ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።
4
ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና፥ ተከናወን፥ ንገሥም፤ ቀኝህም በክብር ይመራሃል።
5
ኀያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ አሕዛብ በበታችህ ይወድቃሉ። በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥
6
አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው፤ በትረ መንግሥትህ የጽድቅ በትር ነው።
7
ጽድቅን ወደድህ፥ ዐመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክህ የደስታ ዘይትን ቀባህ።
8
ከርቤና ሽቱ ዝባድም በልብሶችህ ናቸው።
9
የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
10
ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤
11
ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።
12
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ።
13
ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤ በወርቀ ዘቦ ልብስ የተጐናጸፈችና የተሸፋፈነች ናት።
14
በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሡ ይወስዳሉ፥ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤
15
በደስታና በሐሤት ይወስዱአቸዋል። ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል።
16
በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።
17
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ፤ አቤቱ፥ ስለዚህ ለዓለምና ለዘለዓለም። አሕዛብ ያመሰግኑሃል።
← Chapter 43
Chapter 45 →