bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 28
Psalms 28
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የአማልክት ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፥
2
የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
3
የእግዚአብሔር ቃል በውኆች ላይ ነው። የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ ነው።
4
የእግዚአብሔር ቃል በኀይል ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል በታላቅ ክብር ነው።
5
የእግዚአብሔር ቃል ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
6
እንደ ሊባኖስ ላም ያከሳዋል። ተወዳጅ ግን አንድ ቀንድ እንዳለው ርኤም ልጅ ነው።
7
የእግዚአብሔር ቃል የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
8
የእግዚአብሔር ቃል ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9
የእግዚአብሔር ቃል ዋሊያዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ዛፎችንም ይገልጣል፤ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
10
እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
11
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካቸዋል።
← Chapter 27
Chapter 29 →