bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 29
Psalms 29
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ የጠላቶቼ መዘባበቻ አላደረግኸኝምና አመሰግንሃለሁ።
2
አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ይቅርም አልኸኝ።
3
አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ለይተህ አዳንኸኝ።
4
ጻድቃን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።
5
መቅሠፍቱ ከቍጣው ነውና፥ መዳንም ከፈቃዱ ነውና፤ ማታ ልቅሶ ይሰማል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
6
እኔም በደስታዬ፥ “ለዘለዓለም አልታወክም” አልሁ።
7
አቤቱ፥ በፈቃድህ ለሕይወቴ ኀይልን ስጣት፤ ፊትህን መለስህ፥ እኔም ደነገጥሁ።
8
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ወደ አምላኬም ለመንሁ።
9
ወደ ጥፋት ብወርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ? አፈር ያመሰግንሃልን? ጽድቅህንም ይናገራልን?
10
እግዚአብሔር ሰማ፥ ይቅርም አለኝ፤ እግዚአብሔር ረዳቴ ሆነኝ።
11
ልቅሶዬን መልሰህ ደስ አሰኘኸኝ። ማቄን ቀድደህ ደስታን አስታጠቅኸኝ።
12
ክብሬ እንዲዘምርልህ እንዳልደነግጥም፥ አቤቱ፥ አምላኬ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
← Chapter 28
Chapter 30 →