bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 27
Psalms 27
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
2
በቤተ መቅደስህ እጆችን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
3
ከኃጥኣን ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፤ ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላምን ከሚናገሩ ዐመፅ አድራጊዎች ጋር አትጣለኝ።
4
እንደ ሥራቸውና እንደ ዐሳባቸው ክፋት ስጣቸው፤ እንደ እጃቸውም ሥራ ክፈላቸው፤ ፍዳቸውን በራሳቸው ላይ መልስ።
5
ወደ እግዚአብሔር ሥራ ወደ እጆቹም ተግባር አላሰቡምና አፍርሳቸው፥ አትሥራቸውም።
6
የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን።
7
እግዚአብሔር ረዳቴና መታመኛዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ፥ እርሱም ይረዳኛል፤ ሥጋዬም ለመለመ፥ ፈቅጄም አምነዋለሁ።
8
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፥ ለመሲሑ የመድኀኒቱ መታመኛ ነው።
9
ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥ ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።
← Chapter 26
Chapter 28 →