bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 24
Psalms 24
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
2
አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አልፈር፤ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
3
አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩምና። በከንቱ የሚበድሉ ሁሉ ዘወትር ይፈሩ።
4
አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፤ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
5
በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ አንተ አምላኪዬና መድኀኒቴ ነህና፥ ዘወትርም አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።
6
አቤቱ፥ ቸርነትህን ዐስብ፥ ምሕረትህ ለዘለዓለም ነውና።
7
የልጅነቴን ኀጢአትና ስንፍናየን አታስብብኝ። አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት፥ እንደ ምሕረትህ ዐስበኝ።
8
እግዚአብሔር ቸር ጻድቅም ነው፤ ስለዚህ የሚሳሳቱትን በመንገድ ይመራቸዋል።
9
ለየዋሃን ፍርድን ያስተምራቸዋል፤ ለየዋሃን መንገድን ያመለክታቸዋል።
10
የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ይቅርታና እውነት ነው፤ ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚፈልጉ።
11
አቤቱ፥ ስለ ስምህ ብለህ፥ ኀጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ፥ ብዙ ነውና።
12
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? እርሱ በሚመርጠው መንገድ ይመራዋል።
13
ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14
እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኀይላቸው ነው፥ የእግዚአብሔርም ስም ለሚጠሩት ነው። ሕጉንም ያስተምራቸዋል።
15
ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤ እርሱ እግሮችን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና፥
16
ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም፥ እኔ ብቸኛና ድሃ ነኝና።
17
የልቤ ኀዘን ብዙ ነው፤ ከጭንቀቴ አውጣኝ።
18
ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19
ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥ በግፍም ጥልን ጠልተውኛል።
20
ነፍሴን ጠብቃት አድናትም፥ አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
21
አቤቱ፥ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የዋሃንና ቅኖች ተከተሉኝ።
22
እግዚአብሔር እስራኤልን ከመከራው ሁሉ ያድነዋል።
← Chapter 23
Chapter 25 →