bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 25
Psalms 25
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ እኔ በየዋህነቴ እኖራለሁና ፍረድልኝ፤ እንዳልደክም በእግዚአብሔር አመንሁ።
2
አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፈትን።
3
ምሕረትህ በዐይኔ ፊት ነው፥ በማዳንህም ደስ አለኝ፤
4
በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥ ከዐመፀኞችም ጋር አልገባሁም።
5
የክፉዎችን ማኅበር ጠላሁ፥ ከከዳተኞች ጋር አልቀመጥም።
6
እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፤ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
7
የምስጋናህን ቃል እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
8
አቤቱ፥ የቤትህን ጌጥ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9
ከኀጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አትጣላት።
10
በእጃቸው ተንኮል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃን ተሞልታለች።
11
እኔ ግን በየዋህነቴ እኖራለሁ፤ አቤቱ፦ አድነኝ ይቅርም በለኝ።
12
እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፤ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።
← Chapter 24
Chapter 26 →